Headline News

 

 

 

የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ጉባኤ ሪፖርቶችን ሲያዳምጥ ውሏል፡፡

 

ዛሬ ጧት በክቡር ኢንጅነር ኃይሉ ሻውል የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዚዳንት ንግግር በደማቅ ሥነ ሥርዓት የተከፈተው የፓርቲው ጉባኤ ከሰዓት በኋላም በመቀጠል ከዞኖች የቀረቡ ሪፖርቶችን ሲያዳምጥ ውሏል፡፡


በዚህም መሠረት የከፋ፤ የቦረና፤ የጉጂ፤ የደቡብ ሸዋ፤ የጌዴኦ፤ የሸካ፤ የባሌ፤ የጅማ፤ የምዕራብ ጎጃም፤ የምሥራቅ ሸዋ፤ የሰሜን ሸዋ፤ የሀዊ፤ የምሥራቅ ሐረርጌ፤ የሱማሌ፤ የመተከልና የሌሎችንም ዞኖች ሪፖርቶች አዳምጧል፡፡

በሪፖርቶቹ መካከል ሞረሽ የኪነት ቡድን ልዩ ልዩ አዝናኝና ቀስቃሽ ዜማዎችን በማቅረብ ጉባኤተኛውን አዝናንቷል፡፡

በጠዋቱ የጉባኤ መርሐ-ግብር የጎፋ፤ የጋሞ፤ የወላይታ፤ የሲዳማ፤ የአዋሳ፤ የትግራይ፤ የአፋርና የዳውሮ ዞኖች ተወካዮች ሰፊ ሪፖርቶች አቅርበዋል፡፡

በዚህ ጉባኤ ሂደት ከልዩ ልዩ አገሮች ድጋፍ ሰጪዎች የመልካም ምኞት መግለጫ በማስተላለፍ ላይ የሚገኙ ሲሆን ጉባኤው አሁንም በጉባኤተኞች ንቁ ተሳትፎ ቀጥሏል፡፡

 

 
Disclaimer:- EthioLion does not warrant or assume any legal liability or responsibility for the accuracy, completeness, or usefulness of any information published herein. Information about individual and firm has been supplied by such individual or firm without verification by us .The views and opinions of authors expressed herein do not necessarily state or reflect those of EthioLion editors or those of other opponent parties. The appearance of external hyperlinks does not constitute endorsement by EhtioLion.com of the linked web sites, or the information, products or services contained therein.

Make Ethiolion your homepage

Copyright © 2005 EthioLion All rights reserved