Image

አምልኮ ወይስ ምርኮ?

ተከላካይና ጠባቂ የሌላቸውን ሕፃናት እንዲሁም በኑሯቸው ችግርና ተስፋ መቁረጥ በርሃብና በስራ አጥነት የሚጉላላውን የህብረተሰብ ክፍል ባንዳንድ ጥቃቅን ማባበያ የህብረተሰቡን አምራችና ታዳጊ ሕጻናትን አይምሮአቸውን በማላሸቅ ለሐገርና ለወገን እድገት ንዳያስብ የከንቱ እምነት ሰለባ እንዲሆን ተደርጓል:: በስልጣን ላይ ያለውም መንግስት ሕዝቡን ባልባሌ ባህልና ኅይማኖት ተብትቦ አይምሮውን አደንዝዞ መያዙ ለስልጣኑ መራዘም አስተማማኝነትን ስለሚሰጠው በሕዝባችን ብሩህ ሕይወት በአገር ደህንነትና እድገት ላይ ይህ ነው የማይባል በደል እየፈጸመና እያስፈጸመ ይገኛል: ይህ የባእዳን ማደንዘዣ ሕዝቡን ተብትቦ እንዲይዝለት ጉዳዩን በማበረታታት የጥፋቱ አራማጅ በመሆን እያገለገለ አገራችን ልትወጣው ወደማትችል ባርነትና የባህልና የህብረተሰብ ድቀት እንድትወርድ አገርን ለባእዳን ምርኮ አሳልፎ በመስጠት በገዛ ወገኖቹ ላይ ይህ ነው ተብሎ ሊተመን የማይችል ታላቅ በደል እያደረሰ ነው:: ይህ ሀይማኖት ወይንም እምነት ሳይሆን ህብረተሰቡን ለባዕድ አገርን ለውርደት በመዳረግ ደካማና የተኮላሸ ህብረተሰብ ለማድረግ በምእራባውያን አቀንቃኝነት በመንግስት ተባባሪነት ባገራችን ኢትዮጵያና በሕዝባችን የሚያናደርሱት ታላቅ በደል ዛሬ ታግለን ከአገራችን ምድር በማስወጣት ወደመጣበት ባህር ማዶ ተመልሶ እንዲሄድ ማድረግ ካልቻልን ነገ ላገርና ለወገን ተቆርቋሪ ዜጋ ይኖራል ማለት አዳጋች ነው:: ስለሆነም ይህ በህብረተሰባችን ላይ የሚያደርሱትን ኢሰብአዊ ድርጊት እንደሆነ ታውቆና ታምኖበት አገርንና ወገንን ለማዳን ሁሉም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ይህንን አድራጎት በጥብቅ በማውገዝና ህብረተሰቡንም በማስተማር የሚቻለውን ሁሉ በማድረግ ሊተባበር ይገባል::